ሉቃስ 1:52-56 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

52. ገዢዎችን ከዙፋናቸው አውርዶአቸዋል፤ትሑታንን ግን ከፍ ከፍ አድርጎአቸዋል፤

53. የተራቡትን በበጎ ነገር አጥግቦአቸዋል፤ሀብታሞችን ግን ባዶአቸውን ሰዶአቸዋል፤

54. ምሕረቱን በማስታወስ፣ ባሪያውንእስራኤልን ረድቶአል፤

55. ይህም ለአባቶቻችን እንደ ተናገረ፣ለአብርሃምና ለዘሩ ያለውን ለዘላለም ለመጠበቅ ነው።”

56. ማርያምም ሦስት ወር ያህል ኤልሳቤጥ ዘንድ ከቈየች በኋላ ወደ ቤቷ ተመለሰች።

ሉቃስ 1