ሉቃስ 1:45-49 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

45. ጌታ ይፈጸማል ብሎ የነገራትን ያመነች እርሷ የተባረከች ናት!”

46. ማርያምም እንዲህ አለች፤“ነፍሴ ጌታን ከፍ ከፍ ታደርገዋለች፤

47. መንፈሴም በመድኀኒቴ በእግዚአብሔር ደስ ትሰኛለች፤

48. እርሱ የባሪያውን መዋረድ ተመልክቶአልና።ከዛሬ ጀምሮ ትውልድ ሁሉብፅዕት ይሉኛል፤

49. ኀያል የሆነው እርሱ ታላቅነገር አድርጎልኛልና፤ ስሙም ቅዱስ ነው፤

ሉቃስ 1