ሉቃስ 1:41-54 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

41. ኤልሳቤጥም የማርያምን ሰላምታ በሰማች ጊዜ፣ ፅንሱ በማሕፀኗ ውስጥ ዘለለ፤ ኤልሳቤጥም በመንፈስ ቅዱስ ተሞላች፤

42. ድምፅዋን ከፍ አድርጋ እንዲህ አለች፤ “አንቺ ከሴቶች መካከል የተባረክሽ ነሽ፤ የማሕፀንሽም ፍሬ የተባረከ ነው።

43. ለመሆኑ የጌታዬ እናት ወደ እኔ ትመጣ ዘንድ እኔ ማን ነኝ?

44. እነሆ፤ የሰላምታሽ ድምፅ ጆሮዬ እንደ ገባ፣ በማሕፀኔ ያለው ፅንስ በደስታ ዘሎአልና።

45. ጌታ ይፈጸማል ብሎ የነገራትን ያመነች እርሷ የተባረከች ናት!”

46. ማርያምም እንዲህ አለች፤“ነፍሴ ጌታን ከፍ ከፍ ታደርገዋለች፤

47. መንፈሴም በመድኀኒቴ በእግዚአብሔር ደስ ትሰኛለች፤

48. እርሱ የባሪያውን መዋረድ ተመልክቶአልና።ከዛሬ ጀምሮ ትውልድ ሁሉብፅዕት ይሉኛል፤

49. ኀያል የሆነው እርሱ ታላቅነገር አድርጎልኛልና፤ ስሙም ቅዱስ ነው፤

50. ምሕረቱም ለሚፈሩት ከትውልድእስከ ትውልድ ይኖራል።

51. በክንዱ ብርቱ ሥራ ሠርቶአል፤በልባቸው ሐሳብ የሚታበዩትን በትኖአቸዋል፤

52. ገዢዎችን ከዙፋናቸው አውርዶአቸዋል፤ትሑታንን ግን ከፍ ከፍ አድርጎአቸዋል፤

53. የተራቡትን በበጎ ነገር አጥግቦአቸዋል፤ሀብታሞችን ግን ባዶአቸውን ሰዶአቸዋል፤

54. ምሕረቱን በማስታወስ፣ ባሪያውንእስራኤልን ረድቶአል፤

ሉቃስ 1