ሆሴዕ 9:4-6 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

4. የወይን ጠጅን ቍርባን ለእግዚአብሔር አያፈሱም፤መሥዋዕታቸውም ደስ አያሰኘውም፤እንዲህ ዐይነቱ መሥዋዕት ለእነርሱ የሐዘንተኞች እንጀራ ይሆንባቸዋል፤የሚበሉትም ሁሉ ይረክሳሉ።ይህ ምግብ ለገዛ ራሳቸው ይሆናል፤ወደ እግዚአብሔርም ቤተ መቅደስ አይገባም።

5. በእግዚአብሔር የበዓል ቀናት፣በዓመት በዓሎቻችሁም ቀን ምን ታደርጋላችሁ?

6. ከጥፋት ቢያመልጡም እንኳ፣ግብፅ ትሰበስባቸዋለች፤ሜምፎስም ትቀብራቸዋለች።የብር ሀብታቸውን ዳዋ ያለብሰዋል፤ድንኳኖቻቸውም እሾኽ ይወርሰዋል።

ሆሴዕ 9