ሆሴዕ 5:13-15 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

13. “ኤፍሬም ሕመሙን፣ይሁዳም ቊስሉን ባየ ጊዜ፣ኤፍሬም ወደ አሦር ሄደ፤ርዳታ ለመጠየቅ ወደ ታላቁ ንጉሥ መልእክተኛ ላከ፤እርሱ ግን ሊያድናችሁ፣ቊስላችሁንም ሊፈውስ አይችልም።

14. እኔ ለኤፍሬም እንደ አንበሳ፣ለይሁዳም እንደ ደቦል አንበሳ እሆናለሁና፤ሰባብሬና አድቅቄአቸው እሄዳለሁ፤ነጥቄ እወስዳቸዋለሁ፤ ማንም ሊያድናቸው አይችልም።

15. በደላቸውንም እስኪያውቁ ድረስ፣ወደ ስፍራዬ እመለሳለሁ፤ፊቴን ይሻሉ፤በመከራቸውም አጥብቀውይፈልጉኛል።”

ሆሴዕ 5