ሆሴዕ 5:1-4 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. “እናንተ ካህናት፤ ይህን ስሙ!እናንት እስራኤላውያን፤ አስተውሉ!የንጉሥ ቤት ሆይ፤ ስሙ!ይህ ፍርድ በእናንተ ላይ ነው፤በምጽጳ ወጥመድ፣በታቦርም ላይ የተዘረጋ መረብ ሆናችኋልና።

2. ዐመፀኞች በግድያ በርትተዋል፤ሁሉንም እቀጣቸዋለሁ።

3. ስለ ኤፍሬም ሁሉን ዐውቃለሁ፤እስራኤልም ከእኔ የተሰወረች አይደለችም፤ኤፍሬም፣ አንተ አሁን አመንዝረሃል፤እስራኤልም ረክሳለች።

4. “የሠሩት ሥራ፣ ወደ አምላካቸው እንዲመለሱአይፈቅድላቸውም፤የአመንዝራነት መንፈስ በልባቸው አለ፤ እግዚአብሔርንም አያውቁትም።

ሆሴዕ 5