ሆሴዕ 2:17-20 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

17. የበኣል አማልክትን ስም ከአንደበቷ አስወግዳለሁ፤ከእንግዲህም ስሞቻቸው አይነሡም።

18. በዚያን ቀን ከምድር አራዊትና ከሰማይ ወፎች፣በምድርም ላይ ከሚንቀሳቀሱ ፍጥረት ጋር፣ቃል ኪዳን አደርግላቸዋለሁ፤ሁሉም በሰላም እንዲኖሩ፣ቀስትን፣ ሰይፍንና ጦርነትን፣ከምድሪቱ አስወግዳለሁ።

19. ለእኔ እንድትሆኚ ለዘላለም አጭሻለሁ፤በጽድቅና በፍትሕ፣በፍቅርና በርኅራኄም አጭሻለሁ።

20. በታማኝነት አጭሻለሁ፤አንቺም እግዚአብሔርን ታውቂያለሽ።

ሆሴዕ 2