ሆሴዕ 2:13-17 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

13. ለበኣል አማልክት፣ ዕጣን ስላጠነችባቸው ቀናትእቀጣታለሁ፤በጌጣ ጌጥና በቀለበቶች ራሷን አስጊጣለች፤ውሽሞቿንም ተከትላ ሄዳለች፤እኔን ግን ረስታለች”ይላል እግዚአብሔር።

14. “ስለዚህ እነሆ፤ አባብላታለሁ፤ወደ ምድረ በዳም እወስዳታለሁ፤በፍቅር ቃል አነጋግራታለሁ።

15. በዚያም የወይን ተክሏን እመልስላታለሁ፤የአኮርንም ሸለቆ የተስፋ በር እንዲሆናት አደርጋለሁ።በዚያም ከግብፅ እንደ ወጣችበት ቀን፣እንደ ልጅነቷም ጊዜ ትዘምራለች።

16. “በዚያ ቀን፣ ‘ባሌ’ ብለሽ፣ትጠሪኛለሽ” ይላል እግዚአብሔር።“ከእንግዲህም፣ ‘ጌታዬ’ ብለሽ አትጠሪኝም።

17. የበኣል አማልክትን ስም ከአንደበቷ አስወግዳለሁ፤ከእንግዲህም ስሞቻቸው አይነሡም።

ሆሴዕ 2