3 ዮሐንስ 1:5-8 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

5. ወዳጅ ሆይ፤ ለአንተ እንግዶች ቢሆኑም እንኳ ለወንድሞች በምታደርገው ነገር ሁሉ ታማኝ ነህ።

6. እነርሱ አንተ ስላለህ ፍቅር በቤተ ክርስቲያን ፊት መስክረዋል፤ በመንገዳቸውም እግዚአብሔርን ደስ በሚያሰኝ ሁኔታ ብትረዳቸው መልካም ታደርጋለህ፤

7. ስለ ስሙ የወጡት ከአሕዛብ ምንም ሳይቀበሉ ነውና።

8. እንግዲህ አብረን ለእውነት እንድንሠራ እንዲህ ያሉትን ሰዎች ልናስተና ግድ ይገባናል።

3 ዮሐንስ 1