2 ዜና መዋዕል 8:1-6 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. ሰሎሞን የእግዚአብሔርን ቤተ መቅደስና የራሱን ቤተ መንግሥት የሠራባቸው ሃያ ዓመት ከተፈጸመ በኋላ፣

2. ኪራም የሰጠውን ከተሞች አድሶ እስራኤላውያን እንዲሰፍሩባቸው አደረገ።

3. ከዚያም ሰሎሞን ወደ ሐማት ሱባ ዘመተ፤ ያዛትም።

4. በምድረ በዳውም ውስጥ ተድሞርንና ቀድሞ በሐማት ሠርቶአቸው የነበሩትን የዕቃ ቤት ከተሞች ሁሉ ሠራ።

5. እንዲሁም የላይኛውን ቤት ሖሮንና የታችኛውን ቤትሖሮን የተመሸጉ ከተሞች አድርጎ ከቅጥሮቻቸው፣ ከበሮቻቸውና ከመዝጊያዎቻቸው ጋር ሠራ።

6. ደግሞም ባዕላትንና የዕቃ ቤት ከተሞቹን ሁሉ፣ ሠረገሎችና ፈረሶች የሚኖሩባቸውን ከተሞች ሁሉ፣ ባጠቃላይ በኢየሩሳሌም፣ በሊባኖስና በግዛቱ ሁሉ ለመሥራት የፈለጋቸውን ነገሮች ሁሉ ሠራ።

2 ዜና መዋዕል 8