40. አሁንም አምላኬ ሆይ፤ በዚህ ስፍራ ወደ ቀረበው ጸሎት ዐይኖችህ የተገለጡ፣ ጆሮዎችህም የሚያደምጡ ይሁኑ።
41. “አሁንም እግዚአብሔር አምላክ ሆይ ተነሥ፣ ከኀይልህ ታቦት ጋር ወደ ማረፊያ ቦታህ ግባ። እግዚአብሔር አምላክ ሆይ፤ ካህናትህ ድነትን ይልበሱ፤ ቅዱሳንህም በቸርነትህ ደስ ይበላቸው።
42. እግዚአብሔር አምላክ ሆይ፤ የቀባኸውን አትተወው፤ ለባሪያህ ለዳዊት ቃል የገባህለትን ጽኑ ፍቅር አስብ።