2 ዜና መዋዕል 5:8-11 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

8. ኪሩቤልም ክንፎቻቸውን ከታቦቱ በላይ ባለው ስፍራ ላይ ዘርግተው፣ ታቦቱንና መሎጊያዎቹን ሸፈኑ።

9. መሎጊያዎቹም በጣም ረጃጅም ከመሆናቸው የተነሣ፣ ታቦቱ እስካለበት ድረስ ያሉት ጫፎቻቸው ከቅድስተ ቅዱሳኑ ፊት ለፊት ይታዩ ነበር፤ ከመቅደሱ ውጭ ግን አይታዩም ነበር፤ ዛሬም እዚያው ቦታ ይገኛሉ።

10. እስራኤላውያን ከግብፅ ከወጡ በኋላ ከእነርሱ ጋር ኪዳን ባደረገ ጊዜ፣ ሙሴ በኮሬብ ተራራ በውስጡ ካስቀመጣቸው ከሁለቱ ጽላቶች በቀር በታቦቱ ውስጥ ምንም አልነበረም።

11. ካህናቱም ከቤተ መቅደሱ ወጡ፤ እዚያ የነበሩት ካህናት በምድባቸው መሰረት ባይሆንም፣ ሁሉም ራሳቸውን ቀድሰው ነበር።

2 ዜና መዋዕል 5