2 ዜና መዋዕል 32:32-33 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

32. በሕዝቅያስ ዘመነ መንግሥት የተከናወነው ሌላው ሥራና ቸርነቱ በአሞጽ ልጅ በነቢዩ በኢሳይያስ ራእይ፣ በይሁዳና በእስራኤል ነገሥታት መጽሐፍ ተጽፎአል።

33. ሕዝቅያስም እንደ አባቶቹ ሁሉ አንቀላፋ፤ የዳዊት ዘሮች መካነ መቃብር በሆነው ኰረብታም ተቀበረ። በሞተም ጊዜ ይሁዳ ሁሉና የኢየሩሳሌም ሕዝብ በሙሉ አከበሩት። ልጁ ምናሴም በእርሱ ፈንታ ነገሠ።

2 ዜና መዋዕል 32