2 ዜና መዋዕል 30:1-5 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. ሕዝቅያስ የእስራኤልን አምላክ የእግዚአብሔርን ፋሲካ ለማክበር በኢየሩሳሌም ወዳለው ወደ እግዚአብሔር ቤተ መቅደስ እንዲመጡ፣ ለመላው እስራኤልና ለይሁዳ መልእክት ላከ፤ ለኤፍሬምና ለምናሴም ደብዳቤ ጻፈ።

2. ንጉሡ፣ ሹማምቱና መላው የኢየሩሳሌም ጉባኤ የፋሲካውን በዓል በሁለተኛው ወር ለማክበር ተስማሙ።

3. በቂ ካህናት ራሳቸውን ስላል ቀደሱና ሕዝቡም ገና በኢየሩሳሌም ስላልተ ሰበሰቡ፣ በዓሉን በወቅቱ ለማክበር አልቻሉም ነበር።

4. ንጉሡና መላው ጉባኤም ዕቅዱ ትክክል ሆኖ አገኙት።

5. ስለዚህ የእስራኤልን አምላክ የእግዚአብሔርን ፋሲካ ለማክበር ሕዝቡ እንዲመጣ፣ ከቤርሳቤህ እስከ ዳን ድረስ ዐዋጅ እንዲነገር ወሰኑ፤ በተጻፈው መሠረት በዓሉ ብዛት ባለው ሕዝብ ተከብሮ አያውቅም ነበርና።

2 ዜና መዋዕል 30