8. እንደዚሁም ቅድስተ ቅዱሳኑን ሠራ፤ ርዝመቱ ከቤተ መቅደሱ ወርድ ጋር እኩል ሲሆን፣ ርዝመቱ ሃያ ክንድ፣ ስፋቱም ሃያ ክንድ ነበር፤ ውስጡንም በስድስት መቶ መክሊት የተጣራ ወርቅ ለበጠው።
9. የወርቅ ምስማሮቹም አምሳ ሰቅል ይመዝኑ ነበር፤ የላይኛውንም ክፍሎች እንደዚሁ በወርቅ ለበጠ።
10. በቅድስተ ቅዱሳኑ ውስጥ የሁለት ኪሩቤል ምስል አስቀርጾ በወርቅ ለበጣቸው።
11. ከዳር እስከ ዳር ገጥሞ የተዘረጋው የኪሩቤል ክንፍ በጠቅላላው ሃያ ክንድ ነበር፤ የመጀመሪያው ኪሩብ አንዱ ክንፍ አምስት ክንድ ሆኖ የቤተ መቅደሱን ግድግዳ ሲነካ፣ ሌላው አምስት ክንድ የሆነው ክንፉ ደግሞ የሁለተኛውን ኪሩብ ክንፍ ይነካ ነበር።