6. ኢዮአታም በአምላኩ በእግዚአብሔር ፊት በታማኝነት ስለተመላለሰ፣ እየበረታ ሄደ።
7. በኢዮአታም ዘመነ መንግሥት የተከናወነው ሌላው ተግባር፣ ያደረጋቸው ጦርነቶችና የሠራቸው ነገሮች በሙሉ በእስራኤልና በይሁዳ ነገሥታት መጽሐፍ ተጽፎአል።
8. እርሱም በነገሠ ጊዜ ዕድሜው ሃያ አምስት ዓመት ነበር፤ በኢየሩሳሌም ተቀምጦም ዐሥራ ስድስት ዓመት ገዛ።
9. ኢዮአታም እንደ አባቶቹ ሁሉ አንቀላፋ፤ በዳዊት ከተማ ተቀበረ፤ ልጁ አካዝም በእርሱ ፈንታ ነገሠ።