2 ዜና መዋዕል 22:7-10 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

7. አካዝያስ ኢዮራምን ለመጠየቅ መሄዱን፣ እግዚአብሔር ለአካዝያስ መውደቅ ምክንያት አደረገው፤ አካዝያስ እንደ ደረሰም የናሜሲን ልጅ ኢዩን ለመቀበል ከኢዮራም ጋር ወጣ፤ ኢዩም የአክዓብን ቤት እንዲያጠፋ እግዚአብሔር የቀባው ሰው ነበር።

8. ኢዩ በአክዓብ ቤት ላይ ፍርድ በሚፈጽምበት ጊዜ፣ አካዝያስን ያጅቡ የነበሩትን የይሁዳን መሳፍንትና የዘመዶቹን ወንዶች ልጆች አግኝቶ ገደላቸው።

9. ከዚያም አካዝያስን ለመፈለግ ሄደ፤ የእርሱም ሰዎች አካዝያስን በሰማርያ ከተደበቀበት አግኝተው ያዙት፤ ወደ ኢዩም አምጥተው ገደሉት። “እግዚአብሔርን በፍጹም ልቡ የፈለገው የኢዮሣፍጥ ልጅ ነው” በማለት ቀበሩት። ስለዚህ ከአካዝያስ ቤት የመንግሥቱን ሥልጣን ይይዝ ዘንድ የሚችል ሰው አልነበረም።

10. የአካዝያስ እናት ጎቶልያ ልጇዋ መሞቱን ባየች ጊዜ፣ የይሁዳን ንጉሣውያን ቤተ ሰብ በሙሉ አጠፋች፤

2 ዜና መዋዕል 22