16. እኛም የሚያስፈልግህን ግንድ ሁሉ ከሊባኖስ ቈርጠንና አስረን እስከ ኢዮጴ ድረስ ቍልቍል በማንሳፈፍ እንሰድልሃለን፤ አንተም ወደ ኢየሩሳሌም ታስወስደዋለህ።”
17. ሰሎሞን አባቱ ዳዊት ካደረገው ቈጠራ በኋላ፣ በእስራኤል ምድር የነበሩትን መጻተኞች ሁሉ ቈጠረ፤ ቊጥራቸውም አንድ መቶ አምሳ ሦስት ሺህ ስድስት መቶ ሆነ።
18. ከእነዚህም ሰባ ሺውን ተሸካሚዎች፣ ሰማንያ ሺውን በኰረብታው ላይ ድንጋይ ፈላጮች፣ ሦስት ሺህ ስድስት መቶውን ደግሞ የሥራው ተቈጣጣሪዎች ሆነው ሰዎቹን እንዲያሠሩ መደበ።