2 ዜና መዋዕል 17:1-5 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. ልጁ ኢዮሣፍጥ በእርሱ ፈንታ ነገሠ፤ በእስራኤል ላይ በረታ።

2. እርሱም በተመሸጉት የይሁዳ ከተሞች ሁሉ ውስጥ ወታደር አኖረ፤ እንዲሁም በይሁዳ ምድርና አባቱ አሳ በያዛቸው በኤፍሬም መንደሮች ዘበኞች አስቀመጠ።

3. በለጋነት ዕድሜው አባቱ ዳዊት በሄደበት መንገድ ስለሄደ፣ እግዚአብሔር ከኢዮሣፍጥ ጋር ነበር፤ የበኣልንም አማልክት አልጠየቀም፤

4. ነገር ግን ከእስራኤል ድርጊት ይልቅ፣ የአባቱን ፈለገ፤ ትእዛዛቱንም ተከተለ።

5. እግዚአብሔርም መንግሥቱን በእጁ አጸናለት፤ መላው ይሁዳም ስጦታ አመጣለት፤ ከዚህ የተነሣም ታላቅ ብልጽግናና ክብር አገኘ።

2 ዜና መዋዕል 17