1. ኢዮርብዓም በነገሠ በዐሥራ ስምንተኛው ዓመት አብያ በይሁዳ ነገሠ።
2. በኢየሩሳሌም ተቀምጦም ሦስት ዓመት ገዛ። እናቱ ሚካያ ትባላለች፤ እርሷም የገብዓ ተወላጅ የኡርኤል ልጅ ነበረች።በአብያና በኢዮርብዓምም መካከል ጦርነት ነበር።
3. አብያ አራት መቶ ሺህ ብርቱ ተዋጊዎች ይዞ ዘመተ፤ ኢዮርብዓምም ስምንት መቶ ሺህ ብርቱ ተዋጊዎች ይዞ በመውጣት ጠበቀው።
4. አብያ በኰረብታማው በኤፍሬም አገር በጽማራይም ተራራ ላይ ቆሞ፣ እንዲህ አለ፤ “ኢዮርብዓምና እስራኤል ሁሉ አድምጡኝ!