4. ‘እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ ይህ ነገር ከእኔ ዘንድ ስለ ሆነ፣ ወንድሞቻችሁን ለመውጋት ወደዚያ አትውጡ፤ እያንዳንዳችሁም ወደየቤታችሁ ሂዱ” አላቸው። ስለዚህ ለእግዚአብሔር ቃል በመታዘዝ በኢዮርብዓም ላይ መዝመቱን ትተው ተመለሱ።
5. ሮብዓም መኖሪያውን በኢየሩሳሌም በማድረግ ለመከላከያ የሚሆኑ ከተሞችን በይሁዳ ሠራ፤ እነዚህም
6. ቤተ ልሔም፣ ኤጣም፣ ቴቁሔ፣
7. ቤትጹር፣ ሦኮ፣ ዓዶላም፣
8. ጌት፣ መሪሳ፣ ዚፍ፣
9. አዶራይም፣ ለኪሶ፣ ዓዜቃ፣
10. ጾርዓ፣ ኤሎን፣ ኬብሮን ናቸው። በይሁዳና በብንያም ውስጥ የተመሸጉት ከተሞች እነዚህ ነበሩ።
11. እነዚህንም ምሽጎቻቸውን አጠንክሮ፣ አዛዦችን ሾመባቸው፤ ምግብ፣ ዘይትና የወይን ጠጅ አከማቸባቸው።
12. በየከተሞቹም ሁሉ ጋሻና ጦር አከማችቶ ይበልጥ አጠና ከራቸው። በዚህ ዐይነት ይሁዳንና ቢንያምን የራሱ አደረገ።