2 ዜና መዋዕል 11:3-9 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

3. “ለይሁዳ ንጉሥ ለሰሎሞን ልጅ ለሮብዓምና በይሁዳና በብንያም ላሉ እስራኤላውያን ሁሉ እንዲህ በል፤

4. ‘እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ ይህ ነገር ከእኔ ዘንድ ስለ ሆነ፣ ወንድሞቻችሁን ለመውጋት ወደዚያ አትውጡ፤ እያንዳንዳችሁም ወደየቤታችሁ ሂዱ” አላቸው። ስለዚህ ለእግዚአብሔር ቃል በመታዘዝ በኢዮርብዓም ላይ መዝመቱን ትተው ተመለሱ።

5. ሮብዓም መኖሪያውን በኢየሩሳሌም በማድረግ ለመከላከያ የሚሆኑ ከተሞችን በይሁዳ ሠራ፤ እነዚህም

6. ቤተ ልሔም፣ ኤጣም፣ ቴቁሔ፣

7. ቤትጹር፣ ሦኮ፣ ዓዶላም፣

8. ጌት፣ መሪሳ፣ ዚፍ፣

9. አዶራይም፣ ለኪሶ፣ ዓዜቃ፣

2 ዜና መዋዕል 11