1. ሮብዓም ኢየሩሳሌም በደረሰ ጊዜ፣ እስራኤልን ወግተው መንግሥቱን ወደ ሮብዓም እንዲመልሱ ከይሁዳና ከብንያም ቤት አንድ መቶ ሰማንያ ሺህ ወታደሮች ሰበሰበ።
2. ነገር ግን የእግዚአብሔር ቃል ወደ እግዚአብሔር ሰው ወደ ሸማያ እንዲህ ሲል መጣ፤
3. “ለይሁዳ ንጉሥ ለሰሎሞን ልጅ ለሮብዓምና በይሁዳና በብንያም ላሉ እስራኤላውያን ሁሉ እንዲህ በል፤
4. ‘እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ ይህ ነገር ከእኔ ዘንድ ስለ ሆነ፣ ወንድሞቻችሁን ለመውጋት ወደዚያ አትውጡ፤ እያንዳንዳችሁም ወደየቤታችሁ ሂዱ” አላቸው። ስለዚህ ለእግዚአብሔር ቃል በመታዘዝ በኢዮርብዓም ላይ መዝመቱን ትተው ተመለሱ።
5. ሮብዓም መኖሪያውን በኢየሩሳሌም በማድረግ ለመከላከያ የሚሆኑ ከተሞችን በይሁዳ ሠራ፤ እነዚህም
6. ቤተ ልሔም፣ ኤጣም፣ ቴቁሔ፣