4. “አባትህ በላያችን ከባድ ቀንበር ጫነብን፤ አንተ ግን አስጨናቂውን ሥራና በላያችን የጫነብንን ከባድ ቀንበር አቅልልልን፤ እኛም እንገዛልሃለን።”
5. ሮብዓምም፣ “ከሦስት ቀን በኋላ ተመልሳችሁ ወደ እኔ ኑ” አላቸው፤ ስለዚህ ሰዎቹ ወጥተው ሄዱ።
6. ከዚያም ንጉሥ ሮብዓም፣ “ለዚህ ሕዝብ ምን እንድመልስለት ትመክሩኛላችሁ?” በማለት አባቱ ሰሎሞን በሕይወት ሳለ ያገለገሉትን የእስራኤልን ሽማግሌዎች ጠየቃቸው።
7. እነርሱም፣ “ለእዚህ ሕዝብ ደግ ከሆንህለት፣ ደስ ካሰኘኸውና የሚስማማው መልስ ከሰጠኸው ምንጊዜም ይገዛልሃል” አሉት።