2 ዜና መዋዕል 10:11-15 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

11. አባቴ ከባድ ቀንበር ጫነባችሁ፤ እኔ ግን የባሰ አከብደዋለሁ፤ አባቴ በዐለንጋ ገረፋችሁ፤ እኔ ግን በጊንጥ እገርፋችኋለሁ።”

12. ንጉሡ፣ “ከሦስት ቀን በኋላ ተመልሳችሁ ኑ” ባላቸው መሠረት ኢዮርብዓምና ሕዝቡ ሁሉ ከሦስት ቀን በኋላ ወደ ሮብዓም ተመለሱ።

13. ንጉሡም የሽማግሌዎችን ምክር በመናቅ፣ አመናጭቆ መለሰላቸው፤

14. እርሱም የወጣቶቹን ምክር በመቀበል፣ “አባቴ ቀንበራችሁን አከበደ፤ እኔ ደግሞ የባሰ አከብደዋለሁ፤ አባቴ በአለንጋ ገረፋችሁ፤ እኔ ደግሞ በጊንጥ እገርፋችኋለሁ” አላቸው።

15. እግዚአብሔር በሴሎናዊው በአሒያ አማካይነት ለናባጥ ልጅ ለኢዮርብዓም የተናገረው ቃል ይፈጸም ዘንድ፣ ወስኖ ስለ ነበር፣ ንጉሡ ሕዝቡን አላዳመጠም።

2 ዜና መዋዕል 10