እግዚአብሔር ሆይ፤ አሁንም ጆሮህን አዘንብልና ስማ፤ እግዚአብሔር ሆይ፤ ዐይንህንም ክፈትና እይ፤ ሰናክሬም ሕያው እግዚአብሔርን ይሰድብ ዘንድ የላከውንም ቃል አድምጥ።