2 ነገሥት 12:20-21 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

20. ሹማምቱም በእርሱ ላይ ዐመፁበት፤ ቊልቊል ወደ ሲላ በሚወስደው መንገድ ላይ በቤት ሚሎ ገደሉት።

21. ገዳዮቹ ሹማምትም የሰምዓት ልጅ ዮዛካርና የሾሜር ልጅ ዮዛባት ነበሩ። እርሱም ሞተ፤ እንደ አባቶቹም ሁሉ በዳዊት ከተማ ተቀበረ። ልጁ አሜስያስም በእግሩ ተተክቶ ነገሠ።

2 ነገሥት 12