2 ነገሥት 12:1-3 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. ኢዩ በነገሠ በሰባተኛው ዓመት ኢዮአስ ነገሠ፤ በኢየሩሳሌም ተቀምጦም አርባ ዓመት ገዛ። እናቱ ሳብያ የተባለች፤ የቤርሳቤህ ከተማ ተወላጅ ነበረች።

2. ካህኑ ዮዳሄ ያስተምረው በነበረበት ዘመን ሁሉ፣ ኢዮአስ በእግዚአብሔር ፊት መልካም ነገር አደረገ።

3. ይሁን እንጂ የኰረብታ ማምለኪያ ስፍራዎች አልተወገዱም፤ ሕዝቡም በእነዚህ ቦታዎች መሠዋቱንና ማጠኑን እንደ ቀጠለ ነበር።

2 ነገሥት 12