2 ሳሙኤል 22:32-39 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

32. ከእግዚአብሔር በቀር አምላክ ማን አለና፤ከአምላካችንስ በቀር ዐለት ማን ነው?

33. ኀይልን የሚያስታጥቀኝ፣መንገዴንም የሚያቀና እርሱ አምላኬ ነው።

34. እግሮቼን እንደ ብሆር እግር ያበረታል፤በከፍታዎችም ላይ አጽንቶ ያቆመኛል።

35. እጆቼን ለጦርነት ያሰለጥናል፤ክንዶቼም የናስ ቀስት ይገትራሉ።

36. የማዳንህን ጋሻ ሰጥተኸኛል፤ድጋፍህ ታላቅ አድርጎኛል።

37. እርምጃዬን አሰፋህ፤እግሮቼም አልተሰነካከሉም።

38. “ጠላቶቼን አሳደድሁ፤ አጠፋኋቸውም፤እስኪደመሰሱም ድረስ ወደ ኋላ አልተመለስሁም።

39. ፈጽሜ አጠፋኋቸው፤ ተመልሰውም መቆም አልቻሉም፤ከእግሬም ሥር ወድቀዋል።

2 ሳሙኤል 22