1. አኪጦፌልም፣ አቤሴሎምን እንዲህ አለው፤ “ዐሥራ ሁለት ሺህ ሰው መርጬ፣ በዛሬዪቱ ሌሊት አባትህን አሳድደዋለሁ፤
2. በደከመውና ዐቅም ባነሰው ጊዜም አደጋ እጥልበታለሁ፤ ሽብር እለቅበታለሁ፤ ከዚያም አብሮት ያለው ሕዝብ ሁሉ ትቶት ይሸሻል፤ ንጉሡን ብቻ እመታዋለሁ፣
3. ሕዝቡን ሁሉ ወደ አንተ እመልሳለሁ፣ አንተ የምትፈልገው የአንድ ሰው ብቻ መሞት ሁሉም እንዲመለሱ ያደርጋል። ከዚያም ሕዝቡ ሁሉ በሰላም ይኖራል።”
4. ምክሩም አቤሴሎምንና አብረውት የነበሩትን የእስራኤልን ሽማግሌዎች ሁሉ ደስ አሰኘ።
5. አቤሴሎም ግን፣ “እስቲ ደግሞ አርካዊውን ኩሲን ጥሩትና የሚለውን እንስማ” አለ።
6. ኩሲ ወደ እርሱ በመጣ ጊዜ አቤሴሎም፣ “አኪጦፌል ይህን ምክር አቅርቦአል፤ ታዲያ እርሱ ያለውን እናድርግ? ካልሆነም እስቲ የአንተን ሐሳብ ንገረን” አለው።
7. ኩሲም አቤሴሎምን እንዲህ አለው፤ “አኪጦፌል የሰጠው ምክር በዚህ ጊዜ የሚያዋጣ አይደለም፤