1 ዮሐንስ 5:19-21 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

19. እኛ ከእግዚአብሔር እንደሆንን፣ መላው ዓለምም በክፉው ሥር እንደሆነ እናውቃለን።

20. የእግዚአብሔር ልጅ እንደ መጣ፣ እውነተኛ የሆነውን እርሱን እንድናውቅ ማስተዋልን እንደ ሰጠን እናውቃለን፤ እኛም እውነተኛ በሆነው በልጁ በኢየሱስ ክርስቶስ አለን። እርሱ እውነተኛ አምላክና የዘላለም ሕይወት ነው።

21. ልጆች ሆይ፤ ራሳችሁን ከጣዖቶች ጠብቁ።

1 ዮሐንስ 5