10. ከካህናቱ፦ዮዳኤ፣ ዮአሪብ፣ ያኪን፤
11. የእግዚአብሔር ቤት አለቃ የሆነው የአኪጦብ ልጅ፣ የመራዮት ልጅ፣ የሳዶቅ ልጅ፣ የሜሱላም ልጅ፣ የኬልቅያስ ልጅ ዓዛርያስ።
12. የመልክያ ልጅ፣ የጳስኮር ልጅ፣ የይሮሐም ልጅ ዓዳያ፤ የኢሜር ልጅ፣ የምሺላሚት ልጅ፣ የሜሱላም ልጅ፣ የየሕዜራ ልጅ፣ የዓዲኤል ልጅ መዕሣይ።
13. የቤተ ሰብ አለቃ የነበሩት ካህናት ቍጥር አንድ ሺህ ሰባት መቶ ሥልሳ ነበረ፤ እነዚህም በእግዚአብሔር ቤት ለሚከናወነው አገልግሎት ብቁ ሰዎች ነበሩ።
14. ከሌዋውያን ወገን፦ከሜራሪ ዘሮች የአሳብያ ልጅ፣ የዓዝሪቃም ልጅ፣ የአሱብ ልጅ ሸማያ፣
15. በቅበቃር፣ ኤሬስ፣ ጋላልና የአሳፍ ልጅ፣ የዝክሪ ልጅ፣ የሚካ ልጅ መታንያ።
16. የኤዶታም ልጅ፣ የጋላል ልጅ፣ የሰሙስ ልጅ አብድያ። እንዲሁም በነጦፋውያን ከተሞች የኖረው የሕልቃና ልጅ፣ የአሳ ልጅ በራክያ።