5. ጌራ፣ ሰፉፋ፣ ሒራም።
6. በጌባ ይኖሩ የነበሩትና በኋላም በምርኮ ወደ መናሐት የተወሰዱት የኤሁድ ዘሮች እነዚህ ናቸው፤
7. ናዕማን፣ አኪያ፣ ጌራ፤ በምርኮ ጊዜ እየመራ የወሰዳቸው የዖዛና የአሒሑድ አባት ጌራ ነበረ።
8. ሸሐራይም ሚስቶቹን ሑሺምንና በዕራን ከፈታ በኋላ በሞዓብ ምድር ወንዶች ልጆች ወለደ።
9. ከሚስቱ ከሖዴሽ ዮባብን፣ ዲብያን፣ ማሴን፣ ማልካምን፣
10. ይዑጽን፣ ሻክያንና ሚርማን ወለደ፤ እነዚህም የቤተ ሰብ አለቆች የነበሩ ልጆቹ ናቸው።
11. ሑሺም ከተባለች ሚስቱ አቢጡብና ኤልፍዓል የተባሉ ወንዶች ልጆች ነበሩት።
12. የኤልፍዓል ወንዶች ልጆች፤ዔቤር፣ ሚሻም እንዲሁም ኦኖንና ሎድ የተባሉ ከተሞችን ከነ መንደሮቻቸው የቈረቈረ ሻሜድ፣
13. በኤሎን ይኖሩ ለነበሩ ቤተ ሰቦች አለቆችና የጋት ነዋሪዎችን አስወጥተው ያሳደዱ በሪዓና ሽማዕ።
14. አሒዮ፣ ሻሻቅ፣ ይሬምት፣
15. ዝባድያ፣ ዓራድ፣ ዔድር፣
16. ሚካኤል፣ ይሽጳና ዮሐ የበሪዓ ወንዶች ልጆች ነበሩ።
17. ዝባድያ፣ ሜሱላም፣ ሕዝቂ፣ ሔቤር፣
18. ይሽምራይ፣ ይዝሊያና ዮባብ የኤልፍዓል ወንዶች ልጆች ነበሩ።
19. ያቂም፣ ዝክሪ፣ ዘብዲ፣