1 ዜና መዋዕል 8:34-40 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

34. የዮናታን ወንድ ልጅመሪበኣል፤ እርሱም ሚካን ወለደ።

35. የሚካ ወንዶች ልጆች፤ፒቶን፣ ሜሌክ፣ ታሬዓ፣ አካዝ።

36. አካዝ ይሆዓዳን ወለደ፤ ይሆዓዳም ዓሌሜትን፣ ዓዝሞትን፣ ዘምሪን ወለደ፤ ዘምሪም ሞጻን ወለደ።

37. ሞጻ ቢንዓን ወለደ፤ ቢንዓ ረፋያን ወለደ፤ ረፋያ ኤልዓሣን ወለደ፤ ኤልዓሣም ኤሴልን ወለደ።

38. ኤሴል ስድስት ወንዶች ልጆች ነበሩት፤ ስማቸውም፦ዓዝሪቃም፣ ቦክሩ፣ እስማኤል፣ ሽዓርያ፣ አብድዩ፣ ሐናን ይባላል፤ እነዚህ ሁሉ የኤሴል ልጆች ነበሩ።

39. የወንድሙ የኤሴቅ ወንዶች ልጆች፤ የበኵር ልጁ ኡላም፣ ሁለተኛ ልጁ ኢያስ፣ ሦስተኛ ልጁ ኤሊፋላት።

40. የኡላም ልጆች በቀስት መንደፍ የሚችሉ ብርቱ ተዋጊዎች ነበሩ፤ እነርሱም ባጠቃላይ ቍጥራቸው አንድ መቶ ሃምሳ ወንዶች ልጆችና የልጅ ልጆች ነበሩአቸው፤ እነዚህ ሁሉ የብንያም ትውልዶች ነበሩ።

1 ዜና መዋዕል 8