1 ዜና መዋዕል 8:28-35 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

28. እነዚህ ሁሉ በየትውልድ ሐረጋቸው የተቈጠሩ አለቆችና የቤተ ሰብ መሪዎች ሲሆኑ፣ የሚኖሩትም በኢየሩሳሌም ነበረ።

29. የገባዖን አባት ይዒኤል በገባዖን ኖረ፤ ሚስቱ መዓካ ትባል ነበር።

30. የበኵር ልጁም አብዶን ይባል ነበር፤ የእርሱም ተከታዮች ዱር፣ ቂስ፣ በኣል፣ ኔር፣ ናዳብ፣

31. ጌዶር፣ አሒዮ፣ ዛኩርና

32. የሺምዓ አባት ሚቅሎት ነበሩ። እነዚህም ከሥጋ ዘመዶቻቸው ጋር በኢየሩሳሌም ከተማ አቅራቢያ ይኖሩ ነበር።

33. ኔር ቂስን ወለደ፤ ቂስ ሳኦልን ወለደ፤ ሳኦልም ዮናታንን፣ ሜልኪሳን፣ አሚናዳብን፣ አስበኣልን ወለደ።

34. የዮናታን ወንድ ልጅመሪበኣል፤ እርሱም ሚካን ወለደ።

35. የሚካ ወንዶች ልጆች፤ፒቶን፣ ሜሌክ፣ ታሬዓ፣ አካዝ።

1 ዜና መዋዕል 8