1. ብንያም የበኵር ልጁን ቤላን፣ሁለተኛ ልጁን አስቤልን፣ ሦስተኛ ልጁን አሐራን፣
2. አራተኛ ልጁን ኖሐን፣ አምስተኛ ልጁን ራፋን ወለደ።
3. የቤላ ወንዶች ልጆች እነዚህ ነበሩ፤አዳር፣ ጌራ፣ አቢሁድ፣
4. አቢሱ፣ ናዕማን፣ አሖዋ፣
5. ጌራ፣ ሰፉፋ፣ ሒራም።
6. በጌባ ይኖሩ የነበሩትና በኋላም በምርኮ ወደ መናሐት የተወሰዱት የኤሁድ ዘሮች እነዚህ ናቸው፤
7. ናዕማን፣ አኪያ፣ ጌራ፤ በምርኮ ጊዜ እየመራ የወሰዳቸው የዖዛና የአሒሑድ አባት ጌራ ነበረ።
8. ሸሐራይም ሚስቶቹን ሑሺምንና በዕራን ከፈታ በኋላ በሞዓብ ምድር ወንዶች ልጆች ወለደ።
9. ከሚስቱ ከሖዴሽ ዮባብን፣ ዲብያን፣ ማሴን፣ ማልካምን፣
10. ይዑጽን፣ ሻክያንና ሚርማን ወለደ፤ እነዚህም የቤተ ሰብ አለቆች የነበሩ ልጆቹ ናቸው።
11. ሑሺም ከተባለች ሚስቱ አቢጡብና ኤልፍዓል የተባሉ ወንዶች ልጆች ነበሩት።
12. የኤልፍዓል ወንዶች ልጆች፤ዔቤር፣ ሚሻም እንዲሁም ኦኖንና ሎድ የተባሉ ከተሞችን ከነ መንደሮቻቸው የቈረቈረ ሻሜድ፣
13. በኤሎን ይኖሩ ለነበሩ ቤተ ሰቦች አለቆችና የጋት ነዋሪዎችን አስወጥተው ያሳደዱ በሪዓና ሽማዕ።