1 ዜና መዋዕል 7:21-26 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

21. ልጁ ዛባድ፣ልጁ ሹቱላ።ኤድርና ኤልዓድ ከብቶች ለመስረቅ በወረዱ ጊዜ፣ የአገሩ ተወላጆች በሆኑት በጌት ሰዎች ተገደሉ።

22. አባታቸውም ኤፍሬም ብዙ ቀን አለቀሰላቸው፤ ዘመዶቹም መጥተው አጽናኑት።

23. ከዚያም ወደ ሚስቱ ገብቶ ተኛ፤ እርሷም ፀነሰች፤ ወንድ ልጅም ወለደች፤ በቤተ ሰቡ ላይ ከደረሰው መከራ የተነሣ ስሙን በሪዓ አለው።

24. ሴት ልጁ ስሟ ሲአራ ይባላል፤ እርሷም የታችኛውንና የላይኛውን ቤት ሖሮንንና ኡዜንሼራን የተባሉትን ከተሞች የቈረቈረች ናት።

25. ልጁ ፋፌ፣ ልጁ ሬሴፍ፣ልጁ ቴላ፣ ልጁ ታሐን፣

26. ልጁ ለአዳን፣ ልጁ ዓሚሁድ፣ልጁ ኤሊሳማ፣

1 ዜና መዋዕል 7