1 ዜና መዋዕል 7:16-24 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

16. የሚኪር ሚስት መዓካ ወንድ ልጅ ወለደች፤ ስሙንም ፋሬስ አለችው። የወንድሙም ስም ሱሮስ ይባላል፤ ወንዶች ልጆቹም ኡላምና ራቄም ነበሩ።

17. የኡላም ወንድ ልጅ፤ባዳን፤እነዚህ የምናሴ ልጅ፣ የማኪር ልጅ፣ የገለዓድ ወንዶች ልጆች ናቸው፤

18. እኅቱ መለኬት ኢሱድን፣ አቢዔዝርንና መሕላን ወለደች።

19. የሸሚዳ ወንዶች ልጆች ደግሞ እነዚህ ነበሩ፤አሒያን፣ ሴኬም፣ ሊቅሒ፣ አኒዓም።

20. የኤፍሬም ዘሮች፤ሹቱላ፣ ልጁ ባሬድ፣ልጁ ታሐት፣ ልጁ ኤልዓዳ፣ልጁ ታሐት፣

21. ልጁ ዛባድ፣ልጁ ሹቱላ።ኤድርና ኤልዓድ ከብቶች ለመስረቅ በወረዱ ጊዜ፣ የአገሩ ተወላጆች በሆኑት በጌት ሰዎች ተገደሉ።

22. አባታቸውም ኤፍሬም ብዙ ቀን አለቀሰላቸው፤ ዘመዶቹም መጥተው አጽናኑት።

23. ከዚያም ወደ ሚስቱ ገብቶ ተኛ፤ እርሷም ፀነሰች፤ ወንድ ልጅም ወለደች፤ በቤተ ሰቡ ላይ ከደረሰው መከራ የተነሣ ስሙን በሪዓ አለው።

24. ሴት ልጁ ስሟ ሲአራ ይባላል፤ እርሷም የታችኛውንና የላይኛውን ቤት ሖሮንንና ኡዜንሼራን የተባሉትን ከተሞች የቈረቈረች ናት።

1 ዜና መዋዕል 7