1 ዜና መዋዕል 6:66-70 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

66. ለአንዳንድ የቀዓት ጐሣዎችም ከኤፍሬም ነገድ ድርሻ ላይ የሚኖሩበት ቦታ ተሰጣቸው።

67. በኰረብታማው በኤፍሬም ምድር የሚገኙትን የመማፀኛ ከተሞች ሴኬምን፣ ጌዝርን፣

68. ዮቅምዓምን፣ ቤትሖሮን፣

69. ኤሎንንና ጋትሪሞን ከነመሰማሪያዎቻቸው ሰጧቸው።

70. እንዲሁም እስራኤላውያን ከምናሴ ነገድ እኩሌታ ድርሻ ላይ ዓኔርና ቢልዓም የተባሉትን ከተሞች ከነመሰማሪያዎቻቸው ወስደው ለቀሩት የቀዓት ጐሣዎች ሰጧቸው።

1 ዜና መዋዕል 6