42. የኤታን ልጅ፣ የዛማት ልጅ፣የሰሜኢ ልጅ፣
43. የኢኤት ልጅ፣የጌድሶን ልጅ፣ የሌዊ ልጅ፤
44. በስተግራቸው በኩል አብረዋቸው ያሉት የሜራሪ ልጆች፤የቂሳ ልጅ ኤታን፣ የአብዲ ልጅ፣የማሎክ ልጅ፣
45. የሐሸብያ ልጅ፣የአሜስያስ ልጅ፣ የኬልቅያስ ልጅ፣
46. የአማሲ ልጅ፣ የባኒ ልጅ፣የሴሜር ልጅ፣
47. የሞሖሊ ልጅ፣የሙሲ ልጅ የሜራሪ ልጅ፣የሌዊ ልጅ፣
48. ሌዋውያን ወንድሞቻቸው ግን የእግዚአብሔርን ቤት የማደሪያ ድንኳን ተግባር እንዲያከናውኑ ተመድበው ነበር።