16. የሌዊ ወንዶች ልጆች፤ጌድሶን፣ ቀዓት፣ ሜራሪ።
17. የጌድሶን ወንዶች ልጆች፤ሎቤኒ፣ ሰሜኢ።
18. የቀሃት ወንዶች ልጆች፤እምበረም፣ ይስዓር፣ ኬብሮን፣ ዑዝኤል።
19. የሜራሪ ወንዶች ልጆች፤ሞሖሊ፣ ሙሲ።በየአባቶቻቸው ቤተ ሰብ የተቈጠሩት የሌዊ ጐሣዎች የሚከተሉት ናቸው፤
20. ከጌርሶን፤ልጁ ሎቤኒ፣ ልጁ ኢኤት፣ልጁ ዛማት፣
21. ልጁ ዮአክ፣ልጁ አዶ፣ ልጁ ዛራ፣ ልጁ ያትራይ።
22. የቀዓት ዘሮች፤ልጁ አሚናዳብ፣ ልጁ ቆሬ፣ልጁ አሴር፣
23. ልጁ ሕልቃና፣ልጁ አቢሳፍ፣ ልጁ አሴር፣
24. ልጁ ኢኢት፣ ልጁ ኡርኤል፣ልጁ ዖዝያ፣ ልጁ ሳውል።
25. የሕልቃና ዘሮች፤አማሢ፣ አኪሞት።
26. ልጁ ሕልቃና፣ ልጁ ሱፊ፣ልጁ ናሐት፣
27. ልጁ ኤልያብ፣ልጁ ይሮሐም፣ ልጁ ሕልቃና፣ልጁ ሳሙኤል።
28. የሳሙኤል ወንዶች ልጆች፤የበኵር ልጁ ኢዮኤል፣ሁለተኛው ልጁ አብያ።