15. እግዚአብሔር የይሁዳና የኢየሩሳሌም ሕዝብ በናቡከደነፆር እጅ ተማርከው እንዲወሰዱ ባደረገ ጊዜ ኢዮሴዴቅም አብሮ ተማርኮ ሄደ።
16. የሌዊ ወንዶች ልጆች፤ጌድሶን፣ ቀዓት፣ ሜራሪ።
17. የጌድሶን ወንዶች ልጆች፤ሎቤኒ፣ ሰሜኢ።
18. የቀሃት ወንዶች ልጆች፤እምበረም፣ ይስዓር፣ ኬብሮን፣ ዑዝኤል።
19. የሜራሪ ወንዶች ልጆች፤ሞሖሊ፣ ሙሲ።በየአባቶቻቸው ቤተ ሰብ የተቈጠሩት የሌዊ ጐሣዎች የሚከተሉት ናቸው፤
20. ከጌርሶን፤ልጁ ሎቤኒ፣ ልጁ ኢኤት፣ልጁ ዛማት፣
21. ልጁ ዮአክ፣ልጁ አዶ፣ ልጁ ዛራ፣ ልጁ ያትራይ።