1 ዜና መዋዕል 5:1-5 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. የእስራኤል የበኵር ልጅ የሮቤል ልጆች፤ ሮቤል የበኵር ልጅ ቢሆንም፣ የአባቱን መኝታ ስላረከሰ፣ የብኵርና መብቱ ለእስራኤል ልጅ ለዮሴፍ ልጆች ተሰጥቶአል። ከዚህም የተነሣ ትውልዱ የበኵርነቱን ተራ ይዞ ሊቈጠር አልቻለም።

2. ይሁዳ ከወንድሞቹ ይልቅ ብርቱ ነበረ፤ ገዥ የወጣው ከእርሱ ቢሆንም፣ የብኵርና መብቱ የተላለፈው ለዮሴፍ ነበረ።

3. የእስራኤል የበኵር ልጅ የሮቤል ወንዶች ልጆች፤ሄኖኅ፣ ፋሉሶ፣ አስሮን፣ ከርሚ።

4. የኢዩኤል ዘሮችልጁ ሸማያ፣ ልጁ ጎግ፣ ልጁሰሜኢ፣

5. ልጁ ሚካ፣ልጁ ራያ፣ ልጁ ቢኤል፣

1 ዜና መዋዕል 5