1 ዜና መዋዕል 4:1-4 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. የይሁዳ ዘሮች፤ፋሬስ፣ ኤስሮም፣ ከርሚ፣ ሆር፣ ሦባል።

2. የሦባል ልጅ ራያ ኢኤትን ወለደ፤ ኢኤት ደግሞ አሑማይንና ላሃድን ወለደ፤ እነዚህም የጾርዓውያን ጐሣዎች ናቸው።

3. የኤጣም ወንዶች ልጆች እነዚህ ናቸው፤ ኢይዝራኤል፣ ይሽማ፣ ይደባሽ። እኅታቸው ሃጽሌልፎኒ ትባላለች።

4. ፋኑኤል ጌዶርን ወለደ፤ ኤጽር ደግሞ ሑሻምን ወለደ። እነዚህ የኤፍራታ የበኵር ልጅና የቤተ ልሔም አባት የሆነው የሆር ዘሮች ናቸው።

1 ዜና መዋዕል 4