1 ዜና መዋዕል 26:2-7 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

2. ሜሱላም ወንዶች ልጆች ነበሩት፤የመጀመሪያው ዘካሪያስ፣ሁለተኛው ይዲኤል፣ሦስተኛው ዮዛባት፣አራተኛው የትኒኤል፣

3. አምስተኛው ኤላም፣ስድስተኛው ይሆሐናን፣ሰባተኛው ኤሊሆዔናይ።

4. ዖቤድኤዶምም እንደዚሁ ወንዶችልጆች ነበሩት፤የመጀመሪያው ሸማያ፣ሁለተኛው ዮዛባት፣ሦስተኛው ኢዮአስ፣አራተኛው ሣካር፣አምስተኛው ናትናኤል፣

5. ስድስተኛው ዓሚኤል፣ሰባተኛው ይሳኮር፣ስምንተኛው ፒላቲ፤እግዚአብሔር ዖቤድኤዶምን ባርኮታልና።

6. እንዲሁም ልጁ ሸማያ ወንዶች ልጆች ነበሩት፤ እነርሱም በቂ ችሎታ ስለ ነበራቸው የአባታቸው ቤት መሪዎች ሆነው ነበር።

7. የሽማያ ወንዶች ልጆች፤ ዖትኒ፣ ራፋኤል፣ ዖቤድ፣ ኤልዛባድ፤ ዘመዶቹ ኤሊሁና ሰማክያም እንደዚሁ በቂ ችሎታ ነበራቸው።

1 ዜና መዋዕል 26