እነዚህም ሁሉ የንጉሡ ባለ ራእይ የኤማን ልጆች ነበሩ። እርሱን ከፍ ከፍ እንዲያደርጉትም እግዚአብሔር በገባለት ቃል መሠረት ሰጡት። እግዚአብሔር ለኤማን ዐሥራ አራት ወንዶችና ሦስት ሴቶች ልጆች ሰጠው።