1 ዜና መዋዕል 24:20-27 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

20. ከቀሩት የሌዊ ዘሮች ደግሞ፦ከእንበረም ወንዶች ልጆች፤ ሱባኤል፤ከሱባኤል ወንዶች ልጆች፤ ዬሕድያ።

21. ከረዓብያ ወንዶች ልጆች፤አለቃው ይሺያ።

22. ከይስዓራውያን ወገን፤ ሰሎሚትከሰሎሚት ወንዶች ልጆች፤ ያሐት።

23. የኬብሮን ወንዶች ልጆች፤ የመጀመሪያው ይሪያ፣ ሁለተኛው አማርያ፣ ሦስተኛው የሕዚኤል፣ አራተኛው ይቀምዓም።

24. የዑዝኤል ልጅ፤ ሚካ።ከሚካ ወንዶች ልጆች ሻሚር።

25. የሚካ ወንድም ይሺያ፤ከይሺያ ወንዶች ልጆች ዘካርያስ።

26. የሜራሪ ወንዶች ልጆች፤ ሞሖሊ፣ ሙሲ።የያዝያ ወንድ ልጅ በኖ።

27. የሜራሪ ወንዶች ልጆች፤ከያዝያ በኖ፣ ሾሃም፣ ዘኩር፣ ዔብሪ።

1 ዜና መዋዕል 24