1 ዜና መዋዕል 24:2-17 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

2. ናዳብና አብዩድ ግን ዘር ሳይተኩ ከአባታቸው በፊት ሞቱ፤ ስለዚህ አልዓዛርና ኢታምር ካህናት ሆነው ያገለግሉ ነበር።

3. ዳዊትም የአልዓዛር ዘር የሆነው ሳዶቅና የኢታምር ዘር የሆነው አቢሜሌክ እየረዱት እንደየአገልግሎታቸው ሥርዐት እየለየ መደባቸው።

4. ከኢታምር ይልቅ በአልዓዛር ዘሮች መካከል ብዙ መሪዎች ተገኙ፤ አከፋፈላቸውም እንደሚከተለው ነበር፤ ከአልዓዛር ዘሮች ዐሥራ ስድስት የቤተ ሰብ አለቆች፤ ከኢታምርም ዘሮች ስምንት የቤተ ሰብ አለቆች።

5. ከአልዓዛርና ከኢታምር ዘሮች መካከል የመቅደሱ ሹማምትና የእግዚአብሔር ሹማምት ስለ ነበሩ፣ ያለ አድልዎ በዕጣ ለዩአቸው።

6. የሌዋዊው የናትናኤል ልጅ ጸሓፊው ሸማያ በንጉሡና በሹማምቱ፣ በካህኑ በሳዶቅ፣ በአብያታር ልጅ በአቤሜሌክ እንዲሁም በካህናቱና በሌዋውያኑ ቤተ ሰብ አለቆች ፊት ስማቸውን ጻፈ፤ የጻፈውም አንዱን ቤተ ሰብ ከአልዓዛር ሌላውን ደግሞ ከኢታምር በመውሰድ ነው፤

7. የመጀመሪያው ዕጣ ለዮአሪብ፣ሁለተኛውም ዕጣ ለዮዳሄ ወጣ፤

8. ሦስተኛው ለካሪም፣አራተኛው ለሥዖሪም፣

9. አምስተኛው ለመልክያ፣ስድስተኛው ለሚያሚን፣

10. ሰባተኛው ለአቆስ፣ስምንተኛው ለአብያ፣

11. ዘጠነኛው ለኢያሱ፣ዐሥረኛው ለሴኬንያ፣

12. ዐሥራ አንደኛው ለኤሊያሴብ፣ዐሥራ ሁለተኛው ለያቂም፣

13. ዐሥራ ሦስተኛው ለኦፖ፣ዐሥራ አራተኛው ለየሼብአብ፣

14. ዐሥራ አምስተኛው ለቢልጋ፣ዐሥራ ስድስተኛው ለኢሜር፣

15. ዐሥራ ሰባተኛው ለኤዚር፣ዐሥራ ስምንተኛው ለሃፊጼጽ፣

16. ዐሥራ ዘጠነኛው ለፈታያ፣ሃያኛው ለኤዜቄል፣

17. ሃያ አንደኛው ለያኪን፣ሃያ ሁለተኛው ለጋሙል፣

1 ዜና መዋዕል 24