1 ዜና መዋዕል 24:14-19 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

14. ዐሥራ አምስተኛው ለቢልጋ፣ዐሥራ ስድስተኛው ለኢሜር፣

15. ዐሥራ ሰባተኛው ለኤዚር፣ዐሥራ ስምንተኛው ለሃፊጼጽ፣

16. ዐሥራ ዘጠነኛው ለፈታያ፣ሃያኛው ለኤዜቄል፣

17. ሃያ አንደኛው ለያኪን፣ሃያ ሁለተኛው ለጋሙል፣

18. ሃያ ሦስተኛው ለድላያ፣ሃያ አራተኛ ለመዓዝያ ወጣ።

19. የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ባዘዘውና ከቀድሞ አባታቸው ከአሮን በተሰጣቸው መመሪያ መሠረት ወደ እግዚአብሔር ቤተ መቅደስ በሚገቡበት ጊዜ፣ የተወሰነላቸው ሥርዐት ይህ ነበር።

1 ዜና መዋዕል 24