5. አራቱ ሺህ የቅጥሩ በር ጠባቂዎች ይሁኑ፤ አራቱ ሺህ ደግሞ ለዚሁ ብዬ ባዘጋጀሁት የዜማ መሣሪያ እግዚአብሔርን ያመስግኑ”።
6. ዳዊትም ሌዋውያኑን በሌዊ ልጆች በጌድሶን፣ በቀዓትና በሜራሪ በየጐሣቸው መደባቸው።
7. ከጌድሶናውያን ወገን፤ለአዳን፣ ሰሜኢ።
8. የለአዳን ወንዶች ልጆች፤የመጀመሪያው ይሒኤል፣ ዜቶም፣ ኢዮኤል፤ ባጠቃላይ ሦስት ናቸው።
9. የሰሜኢ ወንዶች ልጆች፤ሰሎሚት፣ ሐዝኤል፣ ሐራን፤ ባጠቃላይ ሦስት ናቸው።እነዚህ የለአዳን ቤተ ሰብ አለቆች ናቸው።
10. የሰሜኢ ወንዶች ልጆች፤ኢኢት፣ ዚዛ፣ የዑስ፣ በሪዓ፤ እነዚህአራቱ የሰሜኢ ልጆች ናቸው።
11. የመጀመሪያው ኢኢት፣ ሁለተኛው ደግሞ ዚዛ ነበረ፤ የዑስና በሪዓ ግን ብዙ ወንዶች ልጆች አልነበሯቸውም፤ ስለዚህ የተቈጠሩት በሥራ መደብ እንደ አንድ ቤተ ሰብ ሆነው ነው።
12. የቀዓት ወንዶች ልጆች፤እንበረም፣ ይስዓር፣ ኬብሮን፣ ዑዝኤል፤ ባጠቃላይ አራት ናቸው።
13. የእንበረም ወንዶች ልጆች፤አሮን፣ ሙሴ።አሮን የተቀደሰ እንዲሆን ተለየ፤ እርሱና ዘሮቹ ለዘላለም ቅዱስ የሆኑትን ነገሮች እንዲቀድሱ፣ በእግዚአብሔር ፊት መሥዋዕት እንዲያቀርቡ፣ በፊቱ እንዲያገለግሉና በስሙም ለዘላለም እንዲባርኩ ተለዩ።
14. የእግዚአብሔር ሰው የሙሴ ወንዶች ልጆችም እንደ ሌዊ ነገድ ሆነው ተቈጠሩ።